Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በዓድዋ የኦሮሞ የጦር አበጋዞች

(ወንደስን ተክሉ)

ዳግማዊ አዒ ምንሊክ የተረከባት ኢትዮጵያ ለ69 ዓመታት በዘመነ መሳፍንት ክፍፍል መዳከም ያላገገመች-ገና ጠንካራማእከላዊ መንግስት ማለትም …[ከ1847 የካቲት 5ቀን ከነገሱት አዒ ቲውድሮስ በሃላ የነገሱት 2ቱ ነገስታት አዒ ተክለጊዮርጊስ እና አዒ ዮሃንስ 4ኛ ጠንካራ ማእከላዊ መንግስት ምስረታ ላይ እንደነበሩ አለፉ እንጂ ገና አልመሰረቱም ነበርና] የጥንቱን የኢትዮጵያ ዳር ድንበርና ግዛትን የተቆጣጠረበት ወቅት አልነበረም ዳግማዊ አዒ ምንሊክ ሲነግሱ። እናም የጥንቱን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ..በአዒ ቲውድሮስ ተጅምሮ እና በአዒ ዮሃንስ የለጠቀውን ዳንር ድንበር የማስከበሩ ታላቅ ታሪካዊ ሃላፊነት በዳግማዊው ምንሊክ ትከሻ ላይ ወደቀ። አጺ ምንሊክም ገና የሸዋ ንጉስ ሆነው ሳለ ጀምሮ በኦሮሞ ሹማምንትና የጦር አበጋዞች የተከበቡ ነበር። ለአብነት ያህልም -ገበየው ጎራ፣ ባልቻ አባነፍሶ፣ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዲ፣አሉላ ብጡል፣ወሊ ብጡልና ራስ ጎበና ዳጪ የሚጠቀሱ ናቸው። የንግስት ጣይቱ ብጡል ወንድሞች አሉላ ብጡል እና ወሊ ብጢል ከዳግማዊ ምንሊክ ጋር የተዋወቁት ሶስቱም በመቅደላ የአጺ ቲውድሮስ እስረኞች በነበሩበት ወቅት ነው። ዳግማዊ ምንሊክ ቀደም ብሎ ከእስር አምልጦ ወደ ሸዋ በመግባት የሸዋ ንጉስ ሆኖ ስለነበረ ወንድማማቾቹም በተራቸው ከመቅደላ እስር ቢት አምልጠው ወደ ሸዋ በመምጣት ምንሊክን ተቀላቀሉ። ወዳጅነታቸውም በእስር ቢት የተጀመረ በመሆኑ በጣም ጥብቅ ነበር። ንግስት ጣይቱ እነዚህን ሁለት ወንድሞቻን ለመጠይቅ ስትመጣ ከምንሊክ ጋር ለመተዋወቅ ቻለች። ንግስት ጣይቱ የኦሮሞ ደም ያለበቸው ሲሆን- የተወለዱትም በዘመነ መሳፍንት ጎንደር ሆኖ ኢትዮጵያን ከገዛው የኦሮሞ ቢተሰብ ከሆነው ከየጁ ሲሩ ጋንጉል ከሚዛመዱ ቢተስብ ነው የተወለዱት። ምንሊክ አጺ ዮሃንስ ሞተው ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ሰፋፊ ግዛት ከያዙት ውስጥ አብዛኞቹ የዮሃንስ ህጋዊ ወራሽ መሆናቸውን አምነው በሰላም ገበሩላቸው። እነሱም-የጎንደር፣የጎጃም፣የወሎ፣የትግራይ፣የኢሉባቦር፣የሲዳማ እና የወለጋ ገዢዎች እና የግቢ ግዛቶችን ወርሮ ያስገበረው የኦሮሞ ንጉስ አባ ጂፋር ነበሩ። የወላጋዎቹ ባላባቶች ኩምሳ ሞረዳ እና ጆቲ ጦርነት ውስጥ ቢገቡ እንደሚሸነፉ ስላወቁና ብሎም የውስጥ አስተዳደር ነጻነታቸው እንደሚከበርላቸው በምንሊክ ቃል ስለተገባላቸው አስተውለው ወሰኑና ለምንሊክ ገቡ። ቃል እንደተገባላቸውም የውስጥ አስተዳደር መብት ተጠበቀላቸው። ምንሊክ ዝም ብለው ወደ አለገበሩ ግዛቶች ሰራዊት አያዘምቱም ነበር በአንጻሩም ደግመው ደጋግመው መልእክት ይልካሉ “እኒ ንጉሰ ነገስትህ ነኝ። አንተም ግባና ግብርሃን አስገባልኝ፣ በግዛትህና በአስተዳደርህ ያንተ ስልጣን ይጸናል” ብለው ይልካል። በመካከላችንም አላስፈላጊ ጦርነት ተነስቶ እልቂት አይፈጠር ሲሉም ለማግባባት ይጥራሉ። በዚህ አቀራረባቸው ብዙዎች ግዛቶችን አስገበሩ እንቢ ካሉትም ጋር ጦር አዝምተው እያሸነፉ እና ያሸነፉትንም አመጸኛ ባላባት ምህረት እየሰጡ መልሰው በተሸነፈበት ግዛቱ ላይ በመሾም አገር ማጠናከሩን ቀጠሉ። የተወሰኑ ባላባቶች ለምሳሊ ይማም መሃመድ ዓሊ [በሃላ የወሎው ንጉስ ሚካኢል የተባለው] ይማም አባዋጠው [የወሎዋ ንግስት መስተዋት ልጅ] መርእድ አዝማች ሃይለሚካኢል እና የሸዋው ደጃዝማች መሸሻ ሰይፉ የትግራዩ ራስ መንገሻ ዮሃንስ እንዲሁም የበጊምድሩና የሰሚኑ ራስ ዘውዲ በምንሊክ ላይ ሁለት እና ሶስት ግዚ እያመጹባቸው በሞት መቀጣት ሲችሉ ምንሊክ ግን ደጋግመው ከማራቸው ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው። የወላይታውን ንጉስ ካኦ ጦና መጠቀስ ያለበት ታሪክ ነው። ንጉስ ጦና በምንሊክ የተላከለትን ሰላማዊ የገብርልኝን ጥሪ ደጋግሞ አልቀበልም በማለት ለመዋጋት የቻለ ነበር። ከምንሊክ ጋር እየተዋጋም ተሽንፎና ክፉኛ ቆስሎ ሊማረክ ቻለ። ምንሊክ ይህን ብዙ ሰራዊታቸውን የፈጀ አመጸኛ በሞት ከመቅጣት ወደራሳቸው አቅርበው-ቁስሉንም አጥበው ምህረት አድርገውለት የወላይታ ንጉስነቱን መልሰው በማጽደቅ ስልጣኑ ላይ በግዛቱ ላይ መልሰው ሾሙት ። ይህ ይቅር ባይነት፣ ትዕግስት እና መሃሪነታቸው ብዙዎን ግዚ አጸፋውን በማስገኘት ግዛታቸውን ሰላማዊ አድርጎላቸዋል። “እምዩ” የሚል ቅጥያ ስምም አሰወጥቶላቸዋል። ምንሊክ በዚህ መልክ የኢትዮጵያን አንድነት አንጻራዊ በሆነ ሰላም እና መረጋጋት በማስተዳደራቸው በ1896 የኢጣሊያን ወራሪ ሰራዊት በዓድዋ ላይ በማያዳግም ሁኒታ ድባቅ ለመምታት ያስቻላቸውን ሕዝባዊ ድጋፍ እና ሃይልን ሊያገኙ በቅተዋል። በዓድዋ ጦርነት ወቅት የምንሊክ ተወዳጅነት ከፍተኛ የሆነበትና አገሪው እምዪ እያለ የሚጠራቸው ወቅት እንደነበረ ታሪክ ጸሃፊያን በገባ አስፍረዋል። በዓድዋው ጦርነት የምንሊክ የጦር አበጋዝ ሆነው ታላቅ ድርሻ ከተወጡት የኦሮሞ ባላባቶች ውስጥ – አባ ጂፋር፣ የወሎው ንጉስ ሚካኢል [ብዙ ግዚ እየሸቱ ግን በንጉሱ ምህረት የተለቀቁ] ራስ አሉላ ብጡል፣ ራስ ወሊ ብጡል፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ [አባ ነፍሶ]ፊታውራሪ ገበየሁ ጎራ፣ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዲ እና ራስ ጎበና ዳጪ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ። እነዚህ ሁሉ ኦሮሞ የጦር አበጋዞችና ባላባቶች ከምንሊክ ጋር ሆነው ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ዳርድንበር ታላቅ ተጋድሎ ለማድረግ ወስነው የተነሱ እና በተግባርም የፈጸሙ ባለታሪክ ናቸው። ሆኖም ትናንሽ ግዛቶች በማእከላዊው መንግስት ስር መጠቃለላቸውን አምርረው የተቃወሙና ያመጹትን ግን ምንሊክና ተባባሪ ባላባቶች እስከሚገዙ ድረስ ቀጥተዋቸዋል። ለምሳሊ የሚጫ እና የአርሲ ኦሮሞዎች ለምንሊክ አልገብርም ብለው በማመጻቸው እስኪገብሩ ድረስ ጦርነት ተካሂዶባቸዋል። እነሱም እጃቸውን አጣጥፈው የተቀመጡ ሳይሆን በጀግንነት ተዋግተዋቸዋል። በምንሊክ ሰራዊትና በእነሱ ተዋጊዎች መካከል ብዙ ጉዳት ደርሳል። በጦርነት ከተሸነፉም በሃላአምነው ምህረት ስላልጠየቁ ምንሊክ በእነሱ ግዛት ላይ የጦር አበጋዞችን ሸመውባቸዋል። ይህ በዘመነ ምንሊክ አገር የመገንባት ትግል ውስጥ የታየ ውስን ክስተት ሲሆን አብዛኛው የአገሪቱ ባላባቶች በሰላማዊው የምንሊክ ጥሪ እየገበሩ በግዛታቸው ውስጥ ግላዊ የአስተዳደር ነጻነታቸው እንደተጠበቀላቸው የገበሩ እንደሆነ አይተናል።

****

ምንጭ- ባሕሩ ዘውዲ ፕ/ር ፍቅሪ ቶሎሳ ጂግሳ

Posted by on February 26, 2017. Filed under አማርኛ/Amharic. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.