Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

“እሸቱን ያየህ ተቀጣ!”

Image result for eshetu alemu

(ክንፉ አሰፋ)

መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ እድሜልክ እስራት ስተፈረዳባቸው

ዘሄግ (14 dec. 17) ዛሬ ዲሴምበር 15 ቀን 2017 ከቀትር በኋላ በሆላንድ ዘሄግ ከተማ የዋለው ችሎት በመቶ አለቃበእሸቱ አለሙ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክስ  እድሜልክ እስራት በይኖባቸዋል። በተጠቀሳባቸው ክስ በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በህዋላ እንዲህ አይነት ፍርድ በሆላንድ ሃገር ሲሰጥ የመጀመርያው መሆኑን አቃቤ ህግ ተናግረዋል። በሃገሪቱ ህግ የእድሜ ልክ እስራት አመክሮ የለውም።

አቶ እሸቱ አለሙ በውሳኔው ሰዓት ችሎቱ ላይ መገኘት አልፈለጉም።

              በአራት ዳኞች በተሰየመው በዚህ International Crime Chamber የተሰኘ  ችሎት የመሃል ዳኛዋ ማርየትሬከንስ የፍርድ ውሳኔውን ባሰሙበት ወቅት አቃቢያን ህጎቹ እና የተበዳይ ጠበቆች በውሳኔው የደስታ ስሜት ታይቶባቸዋል።

              29 ኦክቶበር 2017 ጀምሮ ሲታይ የነበረው ይህ የፍርድ ሂደት የከሳሽ አቃቤ ህግንና የተከሳሽ ጠበቆችን ክርክክርለወር ያህል ሲያዳምጥ ቆይቶ  ውሳኔ ለመስጠት ሳምንት በኋላ ቀጠሮ  ይዞ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ከሁለት አመት በላይ የፈጀው ይህ በአይነቱ ለየት የሚለው፣ የአቶ እሸቱ አለሙ የምርመራ እና የክስ ሂደት አለም አቀፍትኩረትን ስቦ ነበር። ፍርዱ በተሰጠበት በዛሬው እለትም በርካታ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ሃገራት ጋዜጠኞች ወደ ችሎቱታድመዋል።

63 ዓመቱ እሸቱ አለሙ  120 የደርግ አባላት አንዱ ሲሆኑ፣  1970ዎቹ ቀይ ሽብር ዘመን ደርግን ወክለው የጎጃምክፍለ ሃገር አስተዳዳሪ  እንደነበሩ በችሎቱ ፊት ቢመሰክሩም የተመሰረተባቸውን የጦር ወንጀል ክስ ግን ሲቃወሙ ነበር።  

አስራ ሁለት ዓመት ፈጅቶ የነበረው የኢትዮጵያው የቀይ ሽብር ወንጀል ችሎት .. 2006 አቶ እሸቱ አለሙ ላይበሌሉበት የሞት ፍርድ መወሰኑ አይዘነጋም።

1991 ኢህአዴግ ሃገሪቱን ሲቆጣጠር አቶ እሸቱ አለሙ ከነበሩበት ከቡልጋርያ ወደ ሆላንድ በመምጣት የፖለቲካጥገኝነት በመጠየቅ  1992 የሆላንድ መኖርያ ወረቀት ያገኙ ሲሆን አመት በኋላም የሃገሪቱ ዜጋ ሆነዋል። ግለሰቡ   2015 ክመኖርያ ቤታቸው ባላሰቡበት መንገድ ተይዘው ታሰሩ።  ኦክቶበር 29, 2017 – በታሰሩ  2 ዓመት በኋላ – ጉዳዩ በሄግ ችሎትመታየት ጀመረ።

በሆላንድ አቃቤ ህግ የቀረበባቸው ክስ በነሃሴ ወር 1978  75 ወጣቶች ግድያ (በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያንውስጥ ተገድለው በጅምላ የተቀበሩ)  በዘጠኝ ዜጎች ላይ የተደረገ ድብደባ እና የማሰቃየት ወንጀል እና  321 ሰዎች ላይ በደረሰህገወጥ እስራት የሚል ነው።

ለክሶቹ 3000 ገጽ ያላነሰ የጽሁፍ ማስረጃዎች  ፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስልሎች፣  ከኢትዮጵያ፣ ከአሜሪካ፣ ከካናዳእና ከእንግሊዝ የተገኙ  30 በላይ የአይን ምስክሮች ( ከነዚህ ውስት ስምንቱ ምስክሮች ከካናዳ እና ከአሜሪካ ተጉዘው በሄግችሎት በመገኘት  ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን፣  በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ሶስት ባለሙያዎች  (/ ጃን አቢንክ  / ካሳእና ክፉሉ ታደሰበማስረጃነት ቀርበዋል።

Image result for eshetu alemu

Kefelgn Alemu Worku – a notorious prison guard accuse of killing and torturing dozens of people in Ethiopia in the 1970s’ , was sentenced 22 years in prison May 23, 2014

የሆላንድ ፍትህ ሚንስትር በአቶ እሸቱ ላይ ክሱን ለመመስረት መነሻ የሆነው፤   ..1998  ‘ፍራይ ኔደርላንድ‘ (ነጻ ኔዜርላንድበሚል መጽሄት ስለ ተከሳሹ የወጣ ወንጀል ነክ ጽሁፍ ነው።  የሆላንድ አለም ዓቀፍ የወንጀል ምርመራ ቡድንይህንን ጽሁፍ እንደተመለከተ 2009  ጀምሮ የአቶ እሸቱን ስልክ በመጥለፍ መከታተል እንደጀመረ አቃቤ ህግዋ ሚስ ኒኮልፎገለንዛግ ተናግረዋል። 

ይህ ቡድን 2012  ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ የኢዮጵያን መንግስት መረጃ ቢጠይቅም ከመንግስት በኩል ትብብርእንደተነፈገውም አቃቤ ህግዋ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ አልተባበርም ለማለቱ የሰጠው ምክንያት ጉዳዩ በሃገርውስጥ በቀይ ሽብር የወንጀል ችሎት ስላለቀ መቶ አለቃ እሸቱን አሳልፋችሁ ስጡን በሚል ሰበብ ነው።  በሆላንድ እና በኢትዮጵያመካከል የወንጀለኛ ልውውጥ ስምምነት ባለመኖሩ እና በኢትዮጵያ የሞት ፍርድ መሰጠቱ ተጠርጣሪውን የማስረከቡ ጥያቄ ውድቅሊሆን ችሏል። 

አቶ እሸቱ አለሙ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ በተደመጠበት ወቅት “የተሳሳተ ሰው ነው የያዛችሁት”  ብለው ነበር።  ማስረጃዎች ሲቀርቡና የምስክሮች ቃል መሰማት ሲጀምር በወቅቱ አስከፊ ነገር እንደተፈጸመ ተናግረው  ለተፈጠረው ነገር ሁሉ  ይቅርታ ጠይቀዋል። ይሁን እንጂ  እሳቸው በወቅቱ  በፕሮፓጋንዳ ስራ እንደተሰማሩና አንድም  ሰው እንዳልገደሉ፣ ሰውእንዲገደልም ሆነ እንዲታሰር ትዕዛዝ እንዳልሰጡም ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ  የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዳደርግ ፍርድ ቤቱ እድል ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ።  120 የደርግ አባላት  ውስጥ አንዱ ሆኜ ስለተሰራው ወንጀል አዝናለሁ። ግን የቀረቡብኝ ክሶች በሙሉ አልቀበልም።” ብለዋል።

ሺህ አመት  ታሪክ ያላት ሃገራችን እንዳትፈራርስ አሜሪካንን እርዳታ ብንጠይቅ እንቢ ስላሉን ነው ወደ ሶቭየትለመሄድ የተገደድነው።  በወቅቱ የተደራጀው ሃይል ደርግ ብቻ ነው። ኢህአፓ ሃገሪቱን ሊያፈርስ በእብደት የተነሳ ሃይል ነበር። አቶክፍሉ ታደሰ የኢህአፓ አመራር የነበሩ በመሆናቸው ሃሳባቸው ነጻና ገለልተኛ ሊሆን አይችልም።” ሲሉም ኢህአፓን በፍርድ ቤትውሎ ኮንነዋል።

/ ሳንደር አርት፤ የአቶ እሸቱ ጠበቃ የስም መደባለቅን  እንደ  ለመከራከርያ አቅርበው ነበር። ወንጀሉን የፈጸሙትተከሳሹ እሸቱ አለሙ ሳይሆኑ ሌላ እሸቱ ናቸው ሲሉ ተከራክረዋል።

የግድያውን ትዕዛዝ የያዙ ፊርማዎች የሱ ሳይሆኑ የሌላ እሸቱ ናቸው።   ምስክሮቹም የተናገሩት የሚያሳምን አይደለም።የፍርዱ ሂደት ፍትሃዊ አይደለም። አቶ እሸቱ አለሙ 2015 ከቤታቸው ተወስደው ሲታሰሩ ወንጀለኝነታቸው አስቀድሞእንደተረጋገጠ ይተቁማል።” የሚል ነበር የመከራከርያቸው ጭብጥ።

ሌላው የጠበውቃው መከራከርያ ነጥብ ደግሞ  “1978 ጎጃም ውስጥ የርስበርስ ውግያ ባለመካሄዱ ጉዳዩ የጦርወንጀል ሊሆን አይችልም። ተራ ወንጀል ደግሞ በዚህ ችሎት መታየት አይችልም።” የሚል ሲሆን፣  ቀደም ሲል አቶ እሸቱ አለሙበጎጃም ኢህአፓ በተደራጀ መልክ ጦርነት ከፍቶ እንደነበር ለፍርድ ቤቱ የተናገሩት ቃል ይህንን መከራከርያ ነጥብ አፍርሶታል።

የተበዳዮች ጠበቃ የሆኑት ሚስ ባርባራ ፋን ስትራተን – ለእያንዳንዱ ተበዳይ 200 ካሳ ኤሮ እንዲከፈል ፍርድ ቤቱን  ጠይቀዋል። ይህ ካሳ  ምንም እንኳን መጠኑ ዝቅተኛ ቢሆንም ጥፋቱን ለማስረገጥ የተደረግ ተምሳሌታዊ (ሲምቦሊክነውብለዋል።

ከዚህ ቀደም ሁለት የሩዋንዳ እና  አንድ የኢራቅ ተወላጆች ላይ ተመሳሳይ ክስ ተመስርቶ እንዳንዳቸው በ 16 17 አመትእንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል። 

በሆላንድ የእድሜ ልክ እስራት የሚበየነው  እጅግ አስከፊ ለሆነ ወንጀል ስለሆነ  የተመክሮ መብትም የለውም።  በሃገሪቱ እድሜልክ የተፈረደባቸው ሰዎች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።

አቶ እሸቱ አለሙ ባለትዳር እና የሁለት ልጆች የነበሩ ሲሆን ባለቤታቸው እና ልጆቻቸው በውል በማይታወቅ ምክንያትከአመታት በፊት ጥለዋቸው ወደ አሜሪካ በመሄድ ኑሯቸውን እዚያ አድርገዋል። 2015 ከመታሰራቸው በፊት ሆላንዳዊት የትዳርጓደኛቸው ጋር ይኖሩ ነበር።

የአቶ እሸቱ መያዝ እና መታሰር የዚህን ትውልድ  ትኩረት ባይስብም አሁን በሃገሪቱ እየተፈጸመ ላለው ተመሳሳይወንጀል አይን ከፋች ነው።  በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ሰርቶ ከሃገር መውጣት እና መደበቅ እንደማይቻል ትምህርት ይሆናል።  የሆላንድ ፍትህ ሚኒስቴር ያሉትም ይህንኑ ነው።   “ሃገራችን ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች የመደበቅያ ገነትመሆን የለባትም!”

Posted by on December 16, 2017. Filed under አማርኛ/Amharic. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.